አስቸኳይ ማስታወቂያ ለ2ኛ ዲግሪ ነጻ ትምህርት ፈላጊዎች በሙሉ

EORC 1m Telescope

የኢትዩጵያ ስፔስ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ኢንስትዩት በእንጦጦ ኦብዘርቫቶሪና ምርምር ማእከል ከአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ጋር በመተባበር ከ 2007 ዓ.ም. ጀምሮ በ2ኛ እና በ3ኛ ዲግሪ የድህረምረቃ ትምህርት ፕሮግራሞች ሰልጣኞችን ተቀብሎ ስልጠና እየሰጠ መሆኑ የሚታወቅ ሲሆን፣ በ2011 ዓ.ም የትምህርት ዘመን አመልካቾችን በ2ኛ ዲግሪ ተቀብሎ በሚከተሉት የትምህርት መርሀግብሮች የትምህርት ወጪያቸውን ብቻ ሸፎኖ ማስተማር ይፈልጋል

ለ 2ኛ ዲግሪ (M.Sc.)
1ኛ. Astronomy and Astrophysics
2ኛ. Space Science

አመልካቾች ለመመዝገብ የሚከተሉትን መስፈርቶች ማሟላት ይኖርባቸዋል

  • በመጀመሪያ ዲግሪ በፊዚክስ፣ በአስትሮኖሚና አስትሮፊዚክስ፣ በስፔስ ሳይንስ፣ በስፔስ ፊዚክስ፣ በአትሞስፌሪክ ፊዚክስ፣ በኢንስትሩሜንቴሽን፣ በኤሌክትሪካል ኢንጅነሪንግ፣ በሜካኒካል ኢንጂነሪግና በኮምፒዉተር ኢንጂነሪንግ የተመረቀች ወይም የተመረቀ
  • ከላይ በተጠቀሱት የትምህርት መሰኮች ለሴቶች 3.00 ነጥብና ከዛ በላይ የመመረቂያ ውጤት ያላት እና ለወንዶች 3.50ና ከዛ በላይ የመመረቂያ ውጤት ያለው
  • የመመረቂያ የምርምር ስራቸውን ተቋሙ ባዘጋጃቸው የምርምር ፕሮጀክቶችና ምርምሮች ላይ ለመስራት ፈቃደኛ የሆነች/ነ
  • ትምህርታችውን ተቋሙ ባስቀመጠው የትምህርት ማጠናቀቂያ የጊዜ ገደብ ለማጠናቀቅ ፍቃደኛ የሆነች/ነ

አመልካቾች ለምዝገባ ሲመጡ

  • ዋናውን የት/ት ማስረጃችሁንና የማይመለስ 2 ፎቶ ኮፒ፣
  • ሁለት ሪኮመንዴሽን ደብዳቤ፣ ኦፊሻል ትራንስክሪፕት ማስላክ የሚችል
  • በህትመት መፅሄቶች የታተመ የጥናትና ምርምር ስራ ካለ

የመመዝገቢያ ቦታና አድራሻ

የመመዝገቢያ ቦታ፡  6ኪሎ ምስካየ ኀዙናን መድሃኔአለም ቤተክርስቲያን ፊት ለፊት በሚገኘው  አዲሱ የተቋሙ ሬጅስትራር ጽ/ቤት፤

የመመዝገቢያ ጊዜ፡ ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ መስከረም 16 ቀን 2011 ዓ.ም ድረስ ባሉት   ተከታታይ የስራ ቀናት፤

ለመለጠ መረጃ፡- +251-118-72-02-98/+251-118-3324-74 በመደወል ተጨማሪ መረጃ ማግኘት ይቻላል፡፡