አስደሳች ዜና ለ3ኛ እና ለ2ኛ ዲግሪ ትምህርት ፈላጊዎች በሙሉ


የኢትዩጲያ ስፔስ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ኢንስትዩት በእንጦጦ ኦብዘርቫቶሪና ምርምር ማእከል ከአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ጋር በመተባበር ከ 2007 ዓ.ም. ጀምሮ በ2ኛ እና በ3ኛ ዲግሪ የድህረምረቃ ትምህርት ፕሮግራሞች ሰልጣኞችን ተቀብሎ ስልጠና እየሰጠ መሆኑ የሚታወቅ ሲሆን፣በ2011 ዓ.ም የትምህርት ዘመን አመልካቾችን በ2ኛ እና በ3ኛ ዲግሪ በቀን መረሀ ግብር ተቀብሎ በሚከተሉት የትምህርት መርሀግብሮች ለማሰልጠን ዝግጅቱን አጠናቆል፡፡ ስልጠና የሚሰጥባቸው የሙያ ዘርፎች የሚከተሉት ናቸው፡፡

ለ 3ኛ ዲግሪ (PhD) ለ 2ኛ ዲግሪ (M.Sc.)
1ኛ. Astronomy and Astrophysics 1ኛ. Astronomy and Astrophysics
2ኛ. Geodesy and Geodynamics 2ኛ. Remote Sensing
3ኛ. Remote Sensing 3ኛ. Space Science
4ኛ. Space and Atmospheric Science

አመልካቾች ለመመዝገብ የሚከተሉትን መስፈርቶች ማሟላት ይኖርባቸዋል

  • በመጀመሪያ እና በሁለተኛ ዲግሪ በፊዚክስ፣ በአስትሮኖሚና አስተሮፊዚክስ፣ በአፕላይድማቲማቲክስ፣በጂኦፊዚክስ፣ በስፔስሳይንስ፣ በስፔስፊዚክስ፣ በአትሞስፌሪክ ፊዚክስ፣ በኢንስትሩሜንቴሽን፣ በኤሌክትሪካል ኢንጅነሪንግና በኮምፒዉተር ኢንጂነሪንግ፣ሪሞት ሴንሲንግ የተመረቀ
  • የሚሰጠውን የቃልና የጽሁፍ ፈተና ማለፍ የሚችልና ጥሩ የማቲማቲካል፣ የኮምፒውተር ፕሮግራሚንግና የ computational skill ያለው
  • የመመረቂያ የምርምር ስራቸውን በተቋሙ ባዘጋጃቸው የምርምር ፕሮጀክቶችና ምርምሮች ላይ ለመስራት ፈቃደኛ የሆነ
  • ትምህርታችውን ተቁሙ ባስቀመጠው የትምህርት ማጠናቀቂያ የጊዜ ገደብ ለማጠናቀቅ ፍቃደኛ የሆነ
  • አመልካቾች ላመለከቱበት የትምህርት መስክ ለማጠናቀቅ የሚያስፈልገውን የትምህርት ወጪ በራሳቸው ወይም ወጪውን የሚሸፍንላቸው Sponsor ያላቸው መሆን አለባቸው፡፡

አመልካቾች ለምዝገባ ሲመጡ

  • ዋናውን የት/ት ማስረጃችሁንና የማይመለስ 2 ኮፒ፣
  • በተቋሙ የስፖንሰርሺፕ ፎርም ላይ የተሞላ የስፖንሰርሺፕ ደብዳቤ ፣ Download here
  • ሁለት ሪኮመንዴሽን ደብዳቤ፣ ኦፊሻል ትራንስክሪፕት ማስላክ የሚችል
  • ለ 3ኛ ዲግሪ ከ5 ገፅ ያልበለጠ የጥናት የመነሻ ሃሳብ፤ ለ ማስተርስ ተመዝጋቢዎች ከ2 ገፅ ያልበለጠ፤
  • በህትመት መፅሄቶች የታተመ የጥናትና ምርምር ስራ ካለ

የመመዝገቢያ አድራሻ

የመመዝገቢያ ቦታ፡  6ኪሎ ምስካየ ኀዙናን መድሃኔአለም ቤተክርስቲያን ፊት ለፊት በሚገኘው     አዲሱ የተቋሙ ሬጅስትራር ጽ/ቤት፤

መመዝገቢያ ጊዜ፡ ይህማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ ሐምሌ 30 ቀን 2010 ዓ.ም ድረስ ባሉት   ተከታታይ የስራ ቀናት፤

የመግቢያ ፈተና እና የቃል ፈተና ከነሐሴ 9-23 2010 ዓ.ም የሚሰጥ ይሆናል።

በሚከተሉት ስልክ ቁጥሮች በመደወል +251-118-72-02-98/+251-911-1015-01 ተጨማሪ መረጃ ማግኘት ይቻላል፡፡