ለኢትዮጲያ እንድትሰይም የተሰጣትን ኮከብና ፕላኔት ስያሜ አስመልክቶ የተሰጠ መግለጫ


ኢትዮጵያ ከቅርብ ዓመታት ወዲህ በሕዋ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ዘርፍ በምታደርገው ጠንካራተሳትፎ
የአለምአቀፉ የአስትሮኖሚካል ህብረት አባል በመሆን የተለያዩ ሳይንሳዊ ክንውኖችን ከህብረቱ ጋር ስታከናውን
ቆይታለች፡ ይህንኑ ተከትሎ የአለም አቀፉ አስትሮኖሚካል ሕብረት(IAU) የተመሠረተበትን የመቶኛ ዓመት አከባበር
አስመልክቶ ባደረገው የሕዋ ኣካላትን የመሰየም ንቅናቄ የ‹IAU 100 NameExoWorlds› ሃገራችን ኢትዮጵያም
በዚሁ ሂደት ውስጥ አንዷ ተሳታፊ በማድረጉ በአንድሮሜዳ ህብረኮከብ ውስጥ የምትገኘውን በሳይንሳዊ
ኣጠራሯ HD-16175 የተባለች ኣንድ ኮከብንና ይህችን ኮከብ የምትዞራት HD-16175-b የተባለች ዓለምን ያካተተውን
ሥርዓት እንድትሰይም ለሃገራችን ኢትዮጵያ ዕድሉን ሰጥቷል (http://www.nameexoworlds.iau.org/ethiopia) ፡፡ Read here for more…