ለድህረ ምረቃ ትምህርት ፈላጊዎች

  • Post category:News
  • Reading time:2 mins read

ማስታውቂያ

ለድህረ ምረቃ ትምህርት ፈላጊዎች በሙሉ

የስፔስ ሳይንስና ጂኦስፓሻል ኢንስቲዩት ከአዲስ አበባ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርስቲ ጋር በመተባበር በ2015 ትምህርት ዘመን በሁለተኛ እና ሶስተኛ ዲግሪ ተማሪዎችን ተቀብሎ ማስተማር ይፈልጋል፡፡

በሁለተኛ ዲግሪ

  • Master of Science Degree in Space Engineering
  • Master of Science Degree in Aeronautical Engineering

ሶስተኛ ዲግሪ

  • Doctor of Philosophy Degree in Aerospace engineering

የመግቢያ መስፈርት

ለሁለተኛ ዲግሪ

  • በተዛማጅ የትምህርት መስክ ከታወቀ ተቋም የተመረቀ/ች
  • አጠቃላይ ነጥብ ሴት 2.5 እና ለወንድ 2.75 ንጥብ በላይ ያለው ያላት
  • የመግቢያ ፈተና ማለፍ የሚችል/ትችል

ለሶስተኛ ዲግሪ

  • በመጀመሪያ ዲግሪ በተዛማጅ የትምህርት መስክ ከታወቀ ተቋም የተመረቀ/ች
  • ለሁለተኛ ዲግሪ በተዛማጅ የትምህርት መስክ ከታወቀ ተቋም የተመረቀ/ች
  • የሁለተኛ ዲግሪ የመመረቂያ ወጤት ቢያንስ ጥሩ ያለው/ት
  • ለሶስተኛ ዲግሪ ለሚያደረጉት ጥናት ከአምስት ገጽ ያልበለጠ ፕሮፖዛል ማቅረብ የሚችል/የምትችል
  • የመግቢያ ፈተና የሚያልፍ/የምታልፍ
  • የማመልከቻ ጊዜ ከሀምሌ 16 2014 እስከ ሀምሌ 30 2014 ዓ/ም ብቻ

የሚያስፈልጉ ማስረጃዎች

  • የትምህርት ማስረጃ ዲግሪ እና ትራንስክርቢት ዋናውን ፎቶ ኮፒ፤
  • ያለባቸውን የወጪ መጋራት ክፍያ ከፍለው የጨረሱ እና ኦፊሺያል ትራንስክርቢት ከተማሩበት የኒቨርስቲ በምዝገባ ወቅት ማስላክ የሚችሉ፤
  • አራት 3×4 የሆኑ ፎቶግራፎች
  • የስፖንሰርሽፕ ማስረጃ
  • ሞቲቬሽን ደብዳቤ
  • የስራ ልምድ ማስረጃ (ካሎት)
  • የመመዝገቢያ ክፍያ ሁለት መቶ የፈተና 300 መቶ በአጠቃላይ 500 በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ አካውንት ቁጥር 1000007971544 የከፈሉበት ደረስኝ
  • የፈተና ቀን በቀጣይ የምናሳውቅ ይሆናል

አመልካቾች በአዲስ አበባ ስይንስና ቴክኖሎጂ ኢንስቲትዩት ዩኒበርስቲ ድህረ ገጽ ላይ ባዘጋጀው ሊንክ በመከተል ማመልከት ይችላሉ፡፡

http://www.aastu.edu.et/Application/