ኢትዮጵያ የሳተላይት መገጣጠሚያ እና መሞከሪያ ጣቢያ ልትገነባ ነው


የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር፤ ስፔስ ሳይንስና ቴክሎጂ ኢኒስቲቲዩት ከአውሮፓ ኢንቨስትመንት ሃላፊዎች እና ኤርያል ግሩፕ ጋር በመተባበር የሳተላይት መገጣጠሚያ እና መሞከሪያ ጣቢያ በኢትዮጵያ ለመገንባት ተስማምተው እየሰሩ ይገኛሉ፡፡ 3ቱም አካላት ፕሮጀክቱ እስከ አሁን ያለበት ደረጃ የአዋጭነት ጥናት እንዲሁም የአውሮፓ ኢንቨስትመንት ባንክ ለዚህ ፕሮጀክት የሚያግዝበት ሁኔታ ላይ ውይይት አድርገዋል፡፡

ፕሮጀክቱ ሲጠናቀቅና ወደ ስራ ሲገባ በኢትዮጵያ በምስራቅ አፍሪካ ስፔስ ኢንደስትሪ ላይ ትልቅ እገዛ እንደሚዲርግ ተነግሯል፡፡ በፕሮጀክቱ ኢትዮጵያዊያን ኢንጂነሮች የሚሳተፉ ሲሆን የቴክኖሎጂና የእውቀት ሽግግርም ይፈጥራል ተብሎ ይጠበቃል፡፡

ምንጭ የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር
ለበለጠ መረጃ:  http://www.most.gov.et