ከፊል የጨረቃ ግርዶሽ በኢትዮጲያ ሰማይ ላይ


ሐምሌ 9 ቀን፣ 2011 ዓ.ም. በመላው ኣፍሪካ፣ በደቡብ ኣሜሪካ፣ በኣውስትራሊያ፣ በከፊል እስያ፣ በከፊል ኣውሮፓና፣
በከፊል ሰሜናዊ ኣሜሪካ የሚታይ ከፊል የጨረቃ ግርዶሽ ይኖራል፡፡ ግርዶሹ በመላው ኢትዮጲያ የሚታይ ሲሆን ይህ ግርዶሽ ከሌሊቱ 5 ሰዓት ጀምሮ ከሌሊቱ 8 ሰዓት ሲል ይጠናቀቃል፡፡ ይህ ግርዶሽ ከፍተኛ በሚሆንበት ሰዓት ጨረቃ በሰማይ ላይ ደም መስላ የምትታይ ሲሆን ይህ ወቅትም ከሌሊቱ 6 ሰዓት ተኩል ሲል እንደሚታይ ተተንብይዋል፡፡ ይህን ግርዶሽ ለማየት ከመደበኛው የሰው ልጅ የዓይን እይታ ውጪ ምንም ዓይነት ተጨማሪ የሳይንሳዊ ወይም የማጉያ መሣሪያ ኣያስፈልግም፡፡
ለበለጠ መረጃ ይህንን ይጫኑ