የኢትዮጵያ ስፔስ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ኢንስቲትዩት አረንጓዴ አሻራዉን አሳረፈ


የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚንስቴር ከአምስቱ ተጠሪ ተቋማት ጋር በሰሜን ሸዋ ዞን ከአለልቱ ከተማ 30 ኪ.ሜ ርቀት ላይ በምትገኘው ጋራ በሰቃ አካባቢ 17ሺ የሚጠጋ ችግኝ የተከለ ሲሆን የኢ.ስ.ሳ.ቴ.ኢ ሰራተኞችና ተማሪዎችም አረንጓዴ አሻራቸዉን አሳርፈዋል፡፡የተቋሙ ሰራተኞችና ተማሪዎች የችግኝ ተከላ መርሃግብሩ ላይ በመሳተፋቸው ደስተኛ እንደሆኑ ተናግረው “ልጅን ወልዶ ማሳደግ የሚያዉቅበት ማህበረሰብ ስላለን ችግኝም ተክሎ መንከባከብ እንደማይቸገር ” ያላቸዉን እምነት ገልፀዋል፡፡

      

ይህ በእንዲህ እንዳለም በሃገር አቀፍ ደረጃ የ4 ቢሊየን ችግኝ ተከላ ፕሮጀክትን መረጃ የሚያሳይ ድረ-ገፅ ngd.essti.gov.et እና ሃምሌ 22 የአረንጓዴ አሻራ ቀንን አጠቃላይ የተተከለ ችግኝ መረጃ የሚሰጥ ድረ-ገፅ www.greenlegacy.essti.gov.et በኢ.ስ.ሳ.ቴ.ኢ ሃይኮምፒዉቲንግና ዳታ አድሚንስትሬሽን ዲፓርትመንት ተዘጋጅቶ አገልግሎት እየሰጠ እንደሆነ የዲፓርትመንቱ ሃላፊ አቶ መሳይ ወ/ሃና አስታዉቀዋል፡፡