የኢትዮጵያ ስፔስ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ኢንስቲትዩት ከብሄራዊ ሜትሮሎጂ ኤጀንሲ ጋር በጋራ ሊያሰሩ በሚችሉ ጉዳዮች ላይ የስምምነት ሰነድ ተፈራረመ፡፡


የኢትዮጵያ ስፔስ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ኢንስቲትዩት ከብሄራዊ ሜትሮሎጂ ኤጀንሲ ጋር በጋራ ሊያሰሩ በሚችሉ ጉዳዮች ላይ የስምምነት ሰነድ ተፈራረመ፡፡
በሰው ሃይል ግንባታ፤ምርምርና ልማት፤ ምርትና አገልግሎት እንዲሁም የሃብት አጠቃቀምን በተመለከተ የኢትዮጵያ ስፔስ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ኢንስቲትዩት ዋና ዳይሬክተር አቶ አብዲሳ ይልማ እና የብሄራዊ ሜትሮሎጂ ኤጀንሲ ዋና ዳይሬክተር አቶ ፈጠነ ተሾመ የጋራ ስምምነት ሰነድ ተፈራርመዋል፡፡
ከስፔስ ሳይንስና አፕሊኬሽን እንዲሁም ከሪሞት ሴንሲንግ አንፃር ሁለቱ ኢንስቲትዩቶች አለመተባበር እንደማይችሉ የኢትዮጵያ ስፔስ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ኢንስቲትዩት ዋና ዳይሬክተር አቶ አብዲሳ ይልማ ጠቁመው፤ በጋራ ሊያሰሩ የሚችሉ ፕሮጀክቶችን የስትራቴጂክ እቅድ አካል በማድረግ ዉጤት የሚመጣበት አመት እንደሚሆን ገልፀዋል፡፡
የብሄራዊ ሜትሮሎጂ ኤጀንሲ ዋና ዳይሬክተር አቶ ፈጠነ ተሾመ በበኩላቸው በሪሞት ሴንሲንግ የታገዘ ዉጤታማ ስራ መስራት እንደሚቻልና መረጃዎችን በጋራ በመጠቀም መሬት የወረደ ስራ እንደሚሰራ ተናግረዋል፡፡