የዓለም ህዋ ሳምንት ከመስከረም 24 እስከ 30 2013ዓ.ም ድረስ ሊካሄድ ነው


Image may contain: night, text that says 'World Space Week OCTOBER 4-10'

“ሳተላይት ለላቀ ህይወት!” በሚል መሪ ቃል ለተከታታይ 7 ቀናት ሁነት የተዘጋጀ ሲሆን ፤ የኢትዮጵያ ስፔስ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ኢንስቲትዩት አሁን ላይ ያለበት ደረጃና የቀጣይ ትኩረት አቅጣጫ፤ ሳተላይት ለትምህርት ፣ ጤና፣ ግብርና ፣ ኮሙኒኬሽን እንዲሁም ከሳይበር ደህንነት ጋር በተገናኘ ያለዉን ጠቀሜታ የሚዳስስ የግንዛቤ ማስጨበጫ መድረክ በኢንተርኮንቲነታል ሆቴል ለባለድርሻ አካላት የሚዘጋጅ ይሆናል፡፡ በእለቱም ከትምህርት ሚኒስትር፣ ከኢትዮጵያ ቴሌኮሙኒኬሽን፣ ከጤና ሚንስቴር፣ ግብርና ሚንስቴር፣ የኢትዮጵያ ብሮድካስት ባለስልጣን፣ ኢንሳ እና ሌሎች ባለድርሻ አካላት የሚገኙ ይሆናል፡፡

ከዚህ በተጨማሪም የኢ.ስ.ሳ.ቴ.ኢ ሰራተኞች የደም ልገሳና ለጌርጌሴኖን የአእምሮ ህሙማን ማዕከል የበጎ አድራጎት ተግባርም የሚያከናዉኑ ይሆናል፡፡